Tender
ወጋገን ባንክ አ.ማ ለዋናው መ/ቤት ሰራተኞች እንዲሁም ባንኩ በተለያየ ጊዜያቶች ለሚያከናውናቸው ስልጠናዎች ደረጃውን የጠበቀ የካፍቴሪያ እና የሬስቶራንት አገልግሎት ከሚሰጥ ተቋም ጋር በየዓመቱ የሚታደስ የሶስት አመት ውል ለማሰር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Wegagen bank
Deadline 4 Nov 2026
Wednesday, 4 November 2026 · ጥቅምት 25, 2019 ዓ.ም
As stated in the notice: “04/11/2026 03:00”
Original source
Source: reportertenders.com
Open the original notice on reportertenders.com ↗ZaWi HuB shows a copy of this notice. The original notice at the source prevails.
All tender notices come from Reporter Tenders (reportertenders.com), a public tender-notice website, and every notice links to its original page there. ZaWi HuB is a private, independent marketplace and does not represent any government body. Always check the issuing office’s official notice; it prevails over anything shown here.
የጨረታ ቁጥር፡- ወባ/ሰቼማ/031/26
ወጋገን ባንክ አ.ማ ለዋናው መ/ቤት ሰራተኞች እንዲሁም ባንኩ በተለያየ ጊዜያቶች ለሚያከናውናቸው ስልጠናዎች ደረጃውን የጠበቀ የካፍቴሪያ እና የሬስቶራንት አገልግሎት ከሚሰጥ ተቋም ጋር በየዓመቱ የሚታደስ የሶስት አመት ውል ለማሰር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አገልግሎት ሰጪ ተቋማቶች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የመጫረቻ ሰነዳቸውን በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡-
• ተጫራቾች ከጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማኛውም የወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 0736452410101 በመክፈል የገቢ ደረሰኙን ቅጂ በቢሮ ሰዓት ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
• የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው ወጋገን ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 16ተኛ ፎቅ ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት – ግዢ ከፍል መግዛት ይቻላል፡፡
• ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ከማስገባታው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡
• ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
• ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ ለጨረታ ማስከበሪያነት (Bid Security) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ቅድም ሁኔታን ባላካተተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bid Security) ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሚቀርበውም ዋስትና የአገልግሎት ጊዜው (Validity Period) የ90 (ዘጠና) ቀናት ይሆናል፡፡
• ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት የሚያቀርቡት የባንክ ዋስትናም ሆነ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከወጋገን ባንክ ውጭ ከሆኑ ባንኮች መሆን አለበት፡፡
• ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ ዋና፤ የቴክኒካል ሰነድ ቅጂ፤ የፋይናንሻል ሰነድ ዋና፤ የፋይናንሻል ሰነድ ቅጂ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በተለያየ ፖስታዎች በማሸግ 16ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት – ግዢ ከፍል በሚዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ ብቻ በአካል ቀርበው ማስገባት አለባቸው፡፡
• ጨረታው ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
• በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ዝርዝር የተጫራቾች መመሪያ መሰረት ያልቀረበ የመጫረቻ ሰነድ ወይም ተጫራች ከውድድሩ ሊሰረዝ ይችላል፡፡
• ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
Full notice
ወጋገን ባንክ አ.ማ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡- ወባ/ሰቼማ/031/26 ወጋገን ባንክ አ.ማ ለዋናው መ/ቤት ሰራተኞች እንዲሁም ባንኩ በተለያየ ጊዜያቶች ለሚያከናውናቸው ስልጠናዎች ደረጃውን የጠበቀ የካፍቴሪያ እና የሬስቶራንት አገልግሎት ከሚሰጥ ተቋም ጋር በየዓመቱ የሚታደስ የሶስት አመት ውል ለማሰር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አገልግሎት ሰጪ ተቋማቶች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የመጫረቻ ሰነዳቸውን በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡- ተጫራቾች ከጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማኛውም የወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 0736452410101 በመክፈል የገቢ ደረሰኙን ቅጂ በቢሮ ሰዓት ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው ወጋገን ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 16 ተኛ ፎቅ ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት – ግዢ ከፍል መግዛት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ከማስገባታው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ ለጨረታ ማስከበሪያነት (Bid Security) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ቅድም ሁኔታን ባላካተተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bid Security) ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሚቀርበውም ዋስትና የአገልግሎት ጊዜው (Validity Period) የ90 (ዘጠና) ቀናት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት የሚያቀርቡት የባንክ ዋስትናም ሆነ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከወጋገን ባንክ ውጭ ከሆኑ ባንኮች መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ ዋና፤ የቴክኒካል ሰነድ ቅጂ፤ የፋይናንሻል ሰነድ ዋና፤ የፋይናንሻል ሰነድ ቅጂ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በተለያየ ፖስታዎች በማሸግ 16 ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት – ግዢ ከፍል በሚዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ ብቻ በአካል ቀርበው ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ዝርዝር የተጫራቾች መመሪያ መሰረት ያልቀረበ የመጫረቻ ሰነድ ወይም ተጫራች ከውድድሩ ሊሰረዝ ይችላል፡፡ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-12-79 ወይም 011-558-34-07
Source: original notice
