Tender
የዘጠኝ አጋር ድርጅቶች ጥምረት፡ ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH)፣ ብሔራዊ የሴቶች በጎ አድራጎት ድርጅት (NYWCO)፣ የአዲስ አበባ ከተማ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት (AACDCO)፣ ሪዲም ዘ ጄኔሬሽን (RtG)፣ ፌዝ ኢን አክሽን (FIA)፣ ዱካ የወጣቶች መር ድርጅት (DYLO)፣ አይ ኬር ፎር ዘ ኔሽን (ICN)፣ ቤተሳይዳ በጎ አድራጎት ድርጅት (BCO) እና ኢንዱራንስ የወጣቶች ማህበር (EYA) በ ‘Windows of Hope Project 2026’ ስር ለቆዳ እና የጨርቃጨርቅ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት ብቁ፣ የሆኑ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
የዘጠኝ አጋር ድርጅቶች ጥምረት፡ ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH)
Closed 24 Sep 2026
Thursday, 24 September 2026 · መስከረም 14, 2019 ዓ.ም
As stated in the notice: “24/09/2026 04:00”
Original source
Source: reportertenders.com
Open the original notice on reportertenders.com ↗ZaWi HuB shows a copy of this notice. The original notice at the source prevails.
All tender notices come from Reporter Tenders (reportertenders.com), a public tender-notice website, and every notice links to its original page there. ZaWi HuB is a private, independent marketplace and does not represent any government body. Always check the issuing office’s official notice; it prevails over anything shown here.
የልብስ እና የቆዳ ስፌት ማሽን ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የዘጠኝ አጋር ድርጅቶች ጥምረት፡ ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH)፣ ብሔራዊ የሴቶች በጎ አድራጎት ድርጅት (NYWCO)፣ የአዲስ አበባ ከተማ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት (AACDCO)፣ ሪዲም ዘ ጄኔሬሽን (RtG)፣ ፌዝ ኢን አክሽን (FIA)፣ ዱካ የወጣቶች መር ድርጅት (DYLO)፣ አይ ኬር ፎር ዘ ኔሽን (ICN)፣ ቤተሳይዳ በጎ አድራጎት ድርጅት (BCO) እና ኢንዱራንስ የወጣቶች ማህበር (EYA) በ ‘Windows of Hope Project 2026’ ስር ለቆዳ እና የጨርቃጨርቅ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት ብቁ፣ የሆኑ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፓርተር ጋዜጣ ከወጣበት ከጷግሜ 2, 2018ዓም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአጋር ድርጅቶቹ በሚመራው የቴሌግራም ቦት username አድራሻ ማለትም @WoH_bid_portalbot በኩል ወይም በጥምረቱ መሪ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ከጀሞ ሚካኤል ወደ አየርጤና በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን 4ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሃንድ ኢን ሃንድ ቢሮ በአካል መጥተው የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የሚያቀርቡትን ዋጋ ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያ በሃንድ ኢን ሃንድ ሆሊስቲክ ችልድረን ሰርቪስ (HinH) ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው ከመስከረም4 እስከ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓም ከቀኑ 10:00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ተጫራቾች በአንዱ የማሽን አይነት ወይም በሁለቱም መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ለእያንዳንዱ የማሽን አይነት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000.00 ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
የጨረታው ሣጥን መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ጨረታውን አሸንፈው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማያስረክቡ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) በሙሉ ለጥምረቱ አባላት ገቢ ይሆናል።
ጨረታውን ለማያሸንፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል።
ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከሞሉ በሗላ በጥምረቱ መሪ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH) ቢሮ (አድራሻ፡ ጄሞ ሚካኤል፣ ወደ አየርጤና መንገድ 500 ሜትር እንደተጏዙ በሚገኘው ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣ 4ኛ ፎቅ ላይ) በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ገፅ 7 እን 8 ላይ በግልፅ እና በአፅንኦት በተገለጸው መሠረት ለእያንዳንዱ ጥምረት አባል ድርጅት ስም እንደየድርጅቶቹ የማሽን ፍላጎት መሰረት እና ብዛት ራሱን የቻለ በአጠቃላይ 11 የቴክኒክ እና 11 የፋይናንስ ፕሮፖዛሎችን ለየድርጅቶቹ በስማቸው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን የተጫራቾች መመሪያ በትኩረት በመረዳት ተገቢውን የመወዳደሪያ መልስ መሙላት ከተጫራቾች ይጠበቃል። በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች በትክክል አለመሙላት የመወዳደሪያ ውጤቱን ያስቀንሳል::
ጥምረቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
Full notice
የልብስ እና የቆዳ ስፌት ማሽን ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የዘጠኝ አጋር ድርጅቶች ጥምረት፡ ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH)፣ ብሔራዊ የሴቶች በጎ አድራጎት ድርጅት (NYWCO)፣ የአዲስ አበባ ከተማ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት (AACDCO)፣ ሪዲም ዘ ጄኔሬሽን (RtG)፣ ፌዝ ኢን አክሽን (FIA)፣ ዱካ የወጣቶች መር ድርጅት (DYLO)፣ አይ ኬር ፎር ዘ ኔሽን (ICN)፣ ቤተሳይዳ በጎ አድራጎት ድርጅት (BCO) እና ኢንዱራንስ የወጣቶች ማህበር (EYA) በ ‘Windows of Hope Project 2026’ ስር ለቆዳ እና የጨርቃጨርቅ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት ብቁ፣ የሆኑ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፓርተር ጋዜጣ ከወጣበት ከጷግሜ 2, 2018ዓም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአጋር ድርጅቶቹ በሚመራው የቴሌግራም ቦት username አድራሻ ማለትም @WoH_bid_portalbot በኩል ወይም በጥምረቱ መሪ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ከጀሞ ሚካኤል ወደ አየርጤና በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን 4ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሃንድ ኢን ሃንድ ቢሮ በአካል መጥተው የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ። ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የሚያቀርቡትን ዋጋ ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያ በሃንድ ኢን ሃንድ ሆሊስቲክ ችልድረን ሰርቪስ (HinH) ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው ከመስከረም4 እስከ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓም ከቀኑ 10:00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች በአንዱ የማሽን አይነት ወይም በሁለቱም መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ለእያንዳንዱ የማሽን አይነት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000.00 ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: የጨረታው ሣጥን መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታውን አሸንፈው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማያስረክቡ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) በሙሉ ለጥምረቱ አባላት ገቢ ይሆናል። ጨረታውን ለማያሸንፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል። ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከሞሉ በሗላ በጥምረቱ መሪ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH) ቢሮ (አድራሻ፡ ጄሞ ሚካኤል፣ ወደ አየርጤና መንገድ 500 ሜትር እንደተጏዙ በሚገኘው ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣ 4ኛ ፎቅ ላይ) በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ገፅ 7 እን 8 ላይ በግልፅ እና በአፅንኦት በተገለጸው መሠረት ለእያንዳንዱ ጥምረት አባል ድርጅት ስም እንደየድርጅቶቹ የማሽን ፍላጎት መሰረት እና ብዛት ራሱን የቻለ በአጠቃላይ 11 የቴክኒክ እና 11 የፋይናንስ ፕሮፖዛሎችን ለየድርጅቶቹ በስማቸው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው። በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን የተጫራቾች መመሪያ በትኩረት በመረዳት ተገቢውን የመወዳደሪያ መልስ መሙላት ከተጫራቾች ይጠበቃል። በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች በትክክል አለመሙላት የመወዳደሪያ ውጤቱን ያስቀንሳል:: ጥምረቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
Source: original notice
