መከልከል
አዋሽ ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የቀረቡትን መመሪያዎች በመገንዘብ በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
Awash Bank
ተዘግቷል 8 ኦክቶበር 2026
ሐሙስ፣ 8 ኦክቶበር 2026 · መስከረም 28፣ 2019 ዓ.ም
በማስታወቂያው ላይ እንደተገለጸው፡ "08/10/2026 12:42"
ዋና ምንጭ
ምንጭ፡ reportertenders.com
ዋናውን ማስታወቂያ በreportertenders.com ↗ ላይ ይክፈቱZaWi HuB የዚህን ማስታወቂያ ግልባጭ ያሳያል። ምንጩ ላይ ያለው የመጀመሪያው ማስታወቂያ የበላይ ነው።
ሁሉም የጨረታ ማስታወቂያ ከሪፖርተር ጨረታዎች (reportertenders.com)፣ ከሕዝብ የጨረታ ማስታወቂያ ድህረ ገጽ፣ እና እያንዳንዱ ማስታወቂያ እዚያ ካለው የመጀመሪያ ገጽ ጋር ይገናኛል። ZaWi HuB የግል፣ ገለልተኛ የገበያ ቦታ ነው እና የትኛውንም የመንግስት አካል አይወክልም። የአውጪውን ቢሮ ኦፊሴላዊ ማስታወቂያ ሁልጊዜ ያረጋግጡ; እዚህ ከሚታየው ከማንኛውም ነገር በላይ ያሸንፋል።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የቀረቡትን መመሪያዎች በመገንዘብ በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
• ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ሒሳብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዲስ አበባ ከተማ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ሕንፃና የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 1-08 በማቅረብ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
• የጨረታው መነሻ ዋጋዎች እና ሌሎች መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች የሚወዳደርበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም በማሰራትና በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኘውን ቅፅ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዋሽ ባንክ ዋናው መ/ቤት 12ኛ ፎቅ የግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
• ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት አዋሽ ባንክ ዋናው መ/ቤት 12ኛ ፎቅ የግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡
• ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ፤ እንዲሁም ያለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
• የጨረታው አሸናፊዎች ንብረቶቹን ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡
• የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ15(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃለው በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውሰጥ ክፍያውን ፈፅመው ንብረቱን ካልተረከቡ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
• ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
• ተ.ቁ: 1 · የንብረቱ መግለጫ: ሸገር ከተማ፣ ቡራዩ ክ/ከተማ፣ ለኩ ከታ ወረዳ፣ በተለምዶ በግ ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኝ መጋዘን · የንብረቱ ዓይነት: መጋዘን · የቦታ ስፋት: 594.46 ካ.ሜ · ምርመራ: _
• ተ.ቁ: 2 · የንብረቱ መግለጫ: ሸገር ከተማ፣ ቡራዩ ክ/ከተማ፣ ለኩ ከታ ወረዳ፣ በተለምዶ ስማቸው መጋዘን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ መጋዘን · የንብረቱ ዓይነት: መጋዘን · የቦታ ስፋት: 937.89 ካ.ሜ · ምርመራ: _
• ተ.ቁ: 3 · የንብረቱ መግለጫ: አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 09፣ ቂሊንጦ ሳይት ብሎክ 202 ላይ የሚገኝ የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት · የንብረቱ ዓይነት: የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት · የቦታ ስፋት: 57.38 ካ.ሜ · ምርመራ: ሁለቱ ቤቶች በአንድ ላይ ተዋህደው ለጨረታ ቀርበዋል፡፡
• ተ.ቁ: 4 · የንብረቱ መግለጫ: አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 09፣ ቂሊንጦ ሳይት ብሎክ 202 ላይ የሚገኝ የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት · የንብረቱ ዓይነት: የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት · የቦታ ስፋት: 48.50 ካ.ሜ
• ተ.ቁ: 5 · የንብረቱ መግለጫ: ሸገር ከተማ፣ ኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ፣ ቱሉ ዲምቱ ሳይት፣ የሕንፃ ቁጥር 01 ላይ የሚገኝ የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት · የንብረቱ ዓይነት: የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት · የቦታ ስፋት: 95.65 ካ.ሜ · ምርመራ: _
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 530-31-02/04 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
ሙሉ ማስታወቂያ
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አዋሽ ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የቀረቡትን መመሪያዎች በመገንዘብ በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ሒሳብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዲስ አበባ ከተማ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ሕንፃና የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 1-08 በማቅረብ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታው መነሻ ዋጋዎች እና ሌሎች መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች የሚወዳደርበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም በማሰራትና በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኘውን ቅፅ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዋሽ ባንክ ዋናው መ/ቤት 12ኛ ፎቅ የግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት አዋሽ ባንክ ዋናው መ/ቤት 12ኛ ፎቅ የግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ፤ እንዲሁም ያለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ የጨረታው አሸናፊዎች ንብረቶቹን ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡ የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ15(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃለው በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውሰጥ ክፍያውን ፈፅመው ንብረቱን ካልተረከቡ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተ.ቁ የንብረቱ መግለጫ የንብረቱ ዓይነት የቦታ ስፋት ምርመራ 1 ሸገር ከተማ፣ ቡራዩ ክ/ከተማ፣ ለኩ ከታ ወረዳ፣ በተለምዶ በግ ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኝ መጋዘን መጋዘን 594.46 ካ.ሜ _ 2 ሸገር ከተማ፣ ቡራዩ ክ/ከተማ፣ ለኩ ከታ ወረዳ፣ በተለምዶ ስማቸው መጋዘን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ መጋዘን መጋዘን 937.89 ካ.ሜ _ 3 አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 09፣ ቂሊንጦ ሳይት ብሎክ 202 ላይ የሚገኝ የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት 57.38 ካ.ሜ ሁለቱ ቤቶች በአንድ ላይ ተዋህደው ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ 4 አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 09፣ ቂሊንጦ ሳይት ብሎክ 202 ላይ የሚገኝ የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት 48.50 ካ.ሜ 5 ሸገር ከተማ፣ ኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ፣ ቱሉ ዲምቱ ሳይት፣ የሕንፃ ቁጥር 01 ላይ የሚገኝ የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት የንግድ ኮንዶሚንየም ቤት 95.65 ካ.ሜ _ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 530-31-02/04 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
ምንጭ፡- የመጀመሪያ ማስታወቂያ
